የደብረብረሃን ዩንቭርሲቲ በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ስልጠና መስጠት ጀመረ

የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ አዲስ በተቀረጸው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ለመምህራን፣ለአስተዳደርና ቴክኒክ ሰራተኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ ዶ/ር ኃይለማርያም ብርቄ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የዩንቨርሲቲው ተወካይ ፕሬዚዳንት እንዳሉት የዚህ የስልጠና ዋነኛ ዓላማ ሁሉም የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ ለውይይት መነሻነት በተዘጋጁት ጽሁፎች ላይ መሰረት በማድረግ በትምህርትና ስልጠና ችግሮቻችን እንዲሁም በመፍትሔ አቅጣጫዎቹ በቀጣይ ለሚዘጋጀው ፍኖተ-ካርታ ግብዓት ለማሰባሰብ፣በዘላቂ ልማት ግቦች፣በ2010 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማና በ2011 ዓ.ም እቅዶች ላይ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የትምህርት ዘመኑን በውጤታማነት ለመፈጸም ያስችላል ብለዋል፡፡

ስልጠናው ከ1800 በላይ መምህራን፣የአስተዳደርና ቴክኒክ ሰራተኞች በ7 የኃይል መድረኮች ከ40 በላይ በሚሆኑ ቡድኖች ተከፋፍሎ  በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡  

 

CONTACT US

Communications Affairs Directorate 

Tel: +251116816286

Fax- 0116812065

Po.Box: 445

FPR@dbu.edu.et

Nigus Tadese (PhD)

DBU President

JoomShaper