በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ

ደብረብረሃን  ዩኒቨርሲቲ የሥነ- ምግባርና ፀረ- ሙስና ዳይሬክቶሬት የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተቋቋመበትን 20ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በስነምግባር ዙሪያ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ፡፡

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ደረጉት አቶ አህመድ መሀመድ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዳሉት የውድድሩ ዋነኛ አላማ የትውልድ የስነ-ምግባር ግንባታ እሴት ስራ በትውልዱ ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኝ ለማስቻልና የመልካም የስነ-ምግባር ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ጥያቄውን ያዘጋጀው የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የሥነ- ምግባር  ፀረ-ሙስና  ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በደብረብርሃን  ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ በሶስት ቡድኖች ማለትም በዋናው ግቢ/ ሶሻል ሳይንስ፣ግብርና፣ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ህግ፣ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ፣ኮምፒውቲንግ/፣በአስራት ወልደየስ መታሰቢያ ጤና ካምፓስ/ጤና ሳይንስና ህክምና ኮሌጆች/፣በአጼ ሚኒሊክ ቴክኖሎጅ ካምፓስ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ  ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ጀምሮ ተጋባዥ ታዳሚ ተማሪዎች በተገኙበት በግቢ ደረጃ በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄዷል፡፡

የሥነ- ምግባር ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ይሁን ሽፈራው እንዳሉት በተማሪዎች መካከል የተደረገው የተማሪዎች የስነ-ምግባር ጥያቄና መልስ ውድድር አላማው የትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ሂደትን የበለጠ አጉልተው የሚያሳዩ አስተምህሮ ምንነት ግልጽ ለማድረግ እና በዩኒቨርሲው በሚማሩ ተማሪዎች መካከል የስነ-ምግባር ጥያቄና መልስ ውድድር በማካሄድ አሸናፊዎችን በመለየት በዩኒቨርሲቲና በሀገር አቀፍ ደረጃ በመሸለም ተማሪዎችን በማነቃቃት፣ በስነ-ምግባር ዙሪያ የሚኖራቸውን ግንዛቤ እና ተግባራዊነት ድርሻ ለማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጥያቄና መልስ ውድድሩ በቀጣይ ሚያዚያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለሚሄደው ውድድር አሸናፊዎችን በመለየት ተጠናቋል፡፡

 

 

 

JoomShaper