የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በነጥብ የስራ ምዘና በተጠኑ የስራ መደቦች ላይ ያካሄደውን የሰራተኞች ድልድል አጠናቀቀ

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በነጥብ የስራ ምዘና በተጠኑ የስራ መደቦች ላይ ያካሄደውን የሰራተኞች ድልድል መጠናቀቅ አስመልክቶ ከሰራተኞች ጋር የግማሽ ቀን ውይይት ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደጀኔ ጸጋው እንደጠቆሙት የምደባ ሂደቱ ረጅም ጊዜ የወሰደበት ምክንያት ጥናቱ ያልመለሳቸው በርካታ ችግሮች መኖራቸውና ለነዚህም ምላሽ ለማግኘት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡በሌላ በኩል ሰራተኞች በመመሪያው መሰረት መረጃዎችን በአግባቡ አለመሙላታቸውም የራሱ ተጽእኖ ነበረው ብለዋል ፡፡

በስራ ምዘናው 886 ሰራተኞች ያመለከቱ ሲሆን 995 የስራ መደቦች ለውድድር ቀርበው 871 መደቦች ሰራተኛ ተደልድሎባቸዋል፡፡15 ሰራተኞች ለምደባ ካመለከቱ በኋላ የለቀቁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ምደባ ከተሰጣቸው ሰራተኞች መካከል 400(45.9%) በመጀመሪያ ምርጫቸው፣231(26.5) በ2ኛ ምርጫቸው ተመድበዋል፡፡ይህም 631(72.4%)መሆኑ ነው፡፡ቀሪዎቹ ተንሳፋፊ በመሆናቸው ተመሳሳይ ወይም ዝቅ ባለ መደብ እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡በዚህ መሰረት 195(22.4%) በተመሳሳይ መደብ ሲመደቡ፣45(5.2%)ሰራተኞች ዝቅ ባለ መደብ ተመድበዋል፡፡

በቀረበው ማብራሪያ ላይ የተለያዩ የግልጸኝነት ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ምደባው ከሀምሌ 1፣2010 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

CONTACT US

Communications Affairs Directorate 

Tel: +251116816286

Fax- 0116812065

Po.Box: 445

FPR@dbu.edu.et

Nigus Tadese (PhD)

DBU President

JoomShaper