ማስታወቂያ
በደ/ብርሃንዩኒቨርሲቲየ2ኛእናየ3ኛዲግሪትምህርትን ይመለከታል
በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛ (Regular) እና 2ኛዲግሪ በእረፍት ቀናት (Extention) ፕሮግራሞች ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከታች በተዘረዘሩት 43 2ኛ ዲግሪ የትምህርት መስኮች እና በ3ኛ ዲግሪ 1 የት/ት መስክ ተመዝግባችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች ከመስከረም 13/2013 እስከ መስከረም 30/2013 ድረስ በዩኒቨርሲቲው በየኮሌጆች ረጀስትራርና ርቀት ት/ት/ ማስተባበሪያ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መረጃችሁን በማቅረብ ወይም ሰካን የተደረጉ የት/ት ማስረጃዎችንና የክፈያ ሰነዶችን በኢሜል በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡የኮሌጆችን የኢሜል አደራሻ ከዩኒቨርሰቲያችን መረጃ መረብ www.dbu.edu.et ማገኘት ትችላላችሁ፡፡
በምዝገባ ወቅት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
ለማስተርስ
- የመጀመሪያ ዲግሪ Official Transcript- ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ ማሰላክ
- የመጀመሪያ ዲግሪ ሰርተፍኬት ከነትራንስክሪፕቱ ኦርጅናልና የማይመለስ አንዳንድ ኮፒ (ወይም ሰካን የደርገ ኮፒ አስከ መግቢያ ፈተና ድረስ ብቻ የሚገለግል)
- Letter of Sponsorship - ከአሠሪ ተቋም/በመስሪያ ቤት ስፖንሰር ለሚማሩ ተማሪዎች /ፎረሙን ከዩኒቨርስቲችን መረጃ መረብ www.dbu.edu.et ማውረድ እና መሙላት የቻላል/፡፡
ለፒኤችዲ
- የሁለተኛ ዲግሪ Official Transcript- ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲማሰላክ
- የሁለተኛ ዲግሪ ሰርተፍኬት ከነትራንስክሪፕቱ ኦርጅናልና የማይመለስ አንዳንድ ኮፒ (ወይም ሰካን የደርገ ኮፒ አስከ መግቢያ ፈተና ድረስ ብቻ የሚገለግል)
- Letter of Sponsorship - ከአሠሪ ተቋም/በመስሪያ ቤት ስፖንሰር ለሚማሩ ተማሪዎች / ፎረሙን ከዩኒቨርስቲችን መረጃ መረብ www.dbu.edu.et ማውረድ እና መሙላት የቻላል/፡፡
ለሁለቱም ፐሮግራሞች
- ለቅድመ ምዝገባ ማመልከቻ የሚከፈል ብር 80/ሰማኒያ ብር/
- ለመግቢያ ፈተና መቅረቢያ የሚከፈል ብር 80/ሰማኒያ ብር/
የመመዝገቢያ እና የመግቢያ ፈተና ክፍያ በደ/ብ/ዩኒቨርሲቲ በውስጥ ገቢ አካውንት
1000025277515 ገቢ ማድረግ የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን፡፡
- የፈተናው ጊዜ በየኮሌጆቹ በውስጥ ማሰታወቂያ የሚገለጽ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር 011 681 17 71/011 617 08 38
ኮሌጆችን የኢሜል አደራሻ ከዩኒቨርሰቲያችን መረጃ መረብ www.dbu.edu.et ማገኘት ትችላላችሁ፡፡
Download LETTER OF SPONSORSHIP file:-
LETTER OF SPONSORSHIP OF EMPLOYING ORGANIZATION