የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀን ተከበረ

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮምሽን  “ጀግኒት ወንድ ልጇን ስለ ሰብአዊ መብቶች በማስተማር ጾታዊ ጥቃትን ትከላከላለች” በሚል መሪ ቃል የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ ቀንን አክብረዋል፡፡

በዓሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ28ኛ ጊዜ፣በሀገራችን ለ13ኛ ጊዜ በክልላችን ለ9ኛ ጊዜ፣በዩኒቨርሲቲው ለ8ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የዩኒቨርሲቲውን የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት መልዕክት አቅርበዋል፡፡በመልዕክታቸውም ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ መማር ማስተማሩን ለማሳለጥ ጾታዊ ጥቃትን የማይደራደር ማህበረሰብና ተማሪ ለመፍጠር ተግተው እንደሚሰሩ አስታውቀወል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮምሽን ጾታዊ ጥቃት ከሰብዓዊ መብቶች ጋር ያለውን ተዛማጅነት አስመልክቶና ወደፊት ምን እንደሚጠበቅ የሚያወሳ ዳሰሳዊ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በተሳታፊዎችም አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው የፌደራል ሰብዓዊ መብት ኮምሽን የሴቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትሁን ሽፈራው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡  

CONTACT US

Communications Affairs Directorate 

Tel: +251116816286

Fax- 0116812065

Po.Box: 445

FPR@dbu.edu.et

Nigus Tadese (PhD)

DBU President

JoomShaper