እንደተናገሩት ይህ የተማሪዎች ህብረት አመራር ከ10 ሽህ በላይ ተማሪዎችን ወክሎ የሚመረጥ መሆኑን ተናግረው፣ የዩኒቨርሲቲው ምርጫው ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድና የምክር ቤት አባላትም የዩኒቨርሲቲውንና ተማሪዎችን ፍላጎት ተረድተው ይመሩናል፣ያስተዳድሩናል የሚሏቸውን አመራሮች በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲመርጡ አሳስበዋል፡፡
በእለቱ የቀድሞው የተማሪዎች ህብረት ያለፉት ሁለት አመታት ሪፖርት በፕሬዚዳንቱ ከቀረበ በኋላ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡የምክር ቤት አባላትም ካነሷቸው ዋና ዋና ችግሮች መካከል የዩኒቨርሲቲው ክሊኒክ አገልግሎት አሰጣጥና የስነምግባር ችግር እንዲሁም የመድሃኒትና የባለሙያ እጥረቶች፣የዶርሚተሪ ተቆጣጣሪዎች በስራ ቦታ አለመገኘትና በዩኒቨርሲቲው የተከሰተው የውሃ እጥረት፣የንጽህና ጉደለቶች ናቸው፡፡
ለቀረቡት ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል፡፡በእለቱ የመማክርቱ አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ የተመረጡ ሲሆን እጩ ስራ አስፈጻሚዎችም ተጠቁመው የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን አቅርበው 13 አባላት ያሉት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ተካሂዷል፡፡ተጨማሪ 2 አባላት ደግሞ ማለትም የስርዓተ ጾታና የአካል ጉደተኞች ተወካዮች በቀጥታ ከየምክር ቤታቸው የሚወከሉ መሆኑም ታውቋል፡፡
የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ በመዝጊያ ንግግራቸው ባስተላለፉት መልዕክት በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጸጥታ ችግር ምክንያት ችግር ውስጥ በወደቁት ወቅት ዩኒቨርሰቲው እንዲበጠበጥ ጥረት በነበረበት ወቅት ነባሩ የተማሪዎች ህብረት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር አንድም የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ለበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡አዲሱ የተማሪዎች ህብረት መብት ተኮር ብቻ ሳይሆን መብትና ግዴታውን አውቆ እንዲሰራ እንዲሁም ጥቃቅን ችግሮችን ከመራገብ ይልቅ መፍትሄ የሚሰጥ አካል መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ተመራጭ የምክር ቤት አባላት ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል፡፡የስራ ጊዜአቸውን ላጠናቀቁ የህብረቱ የስራ አስፈጻሚ አባለት የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡