Notice
በጉባዔው መክፈቻ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሽህ ዘመናት የበለጸገ ስልጡን ታሪክ፣አኩሪ የነጻነት ተጋድሎ፣ ዘመን ተሸጋሪ ኪነጥበባት፣የማይነጥፉ የዕውቀት ምንጮችና ቱባ የማንነት መገለጫ ባህሎች ያሏት ስትሆን እነዚህን እሴቶች ለቀጣይ ተውልዶች ለማስተላለፍ የእውቀት ማዕከላት የሆኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጥናትና ምርምር በመታገዝ ለቀጣይ ትውልድ ማሰተላለፍ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ፕሬዚዳንቷ አክለው እንደተናገሩት የተከበረው ኢትዮጵያዊ ባህላችን ለሰላም፣ለሉዓላዊ ሃገራዊ አንድነት ግንባታ፣ለአብሮነት፣መከባበርና ፍቅር ማሳያ የሚሆኑ የዳበሩ ትውፊቶች ያሉት፡ከጸብ ይልቅ ለፍቅርና ለሌላው ቅድሚያ መስጠትን ያፀና ልማድ አለው ብለዋል፡፡
በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ በመገኘት የጉባኤውን መክፈቻ ቁልፍ ሀሳብ ያቀረቡት ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር እንዳሉት ባህልና ኪነጥበብ ረጅም የታሪክ ዘመን ያላቸው፣ከሰው ልጆች ጥንታዊ አመጣጥ ጋር የተገናኙ፣የሰውን ልጅ በታሪክ ዘመን ሁሉ በአንድነት እንዲኖር ያስቻሉ ዘርፎች ሆነው እንመለከታቸዋለን ብለዋል፡፡ሚኒስትሯ አክለው አንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲዎች የትንሽዋ ኢትዮጵያ ወካይ በመሆናቸው የተለያዩ ባህሎች የሚንጸባረቁባቸው፣የአብሮነት፣የመቻቻል፣የሰላምና የፍቅር ተምሳሌቶቻችን በመሆናቸው እዚህ የምንገነባው እሴት ፍሬው ለሀገር ይበቃል ብለዋል፡፡ስለሆነም ባህልና ኪነጥበብን፣ለመማር ማስተማር፣ለጥናትና ምርምር፣ለማህበረሰብ አገልግሎት፣ከፍተኛውን ሚና እንዲጫዎቱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የጋራ ኃላፊነት አለባቸው በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሁለተኛው የጉኤው ቁልፍ ንግግር አቅራቢ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ሲሆኑ በባህልና ስነጥበብ ፋይዳ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡እንደ ምሁሩ ገለጻም ባህል የሰውን ልጅ ከህገ ተፈጥሮ ወደ ስልጣኔ ይወሰዳል ብለዋል፡፡
በሁለት ትይዩ መርሃ-ግብሮች ሲያከሂድ የቆየው ጉባዔ ጥናትና ምርምር ላቀረቡና የላቀ ተሳትፎ ላበረከቱ አካላት የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል፡፡