Notice
አጠቃላይ የተማሪ አገልግሎቶች ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረግ ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ መደላድል በመፍጠር ተማሪዎቹ ስለዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ግንዛቤ ጨብጠው ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ የቅድመ ትምህርት ግንዛቤ ፈጠሯል፡፡
የደብረብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ.ር ደረጀ አንዳርጌ ለተማሪዎቹ እንደተናገሩት ከቤተሰቦቻችሁ እቅፍ ወጥታችሁ ወደዚህች ጥንታዊትና ታሪካዊ ከተማ ደብረብረብርሃን እንዲሁም ወደ ዩኒቨርሲቲያችን እንኳን በደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን በደብረብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመመደባችሁም በጣም ደስ ብሎናል ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አክለውም እኛ አባትም እናትም ሆነን ልናገለግላችሁ ቆርጠን ተዘጋጅተናል ያሉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲያችን የቦርድ ስራ አመራር አባል በመካከላችሁ ተገኝተው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለታቸውና ልምዳቸውን ስለሚያካፍሏችሁ እድለኞች ያደርጋችኋል ብለዋል፡፡
የደብረብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ.ር ደረጀ አጅቤ ከቤተሰብ እጅ ወጥታችሁ እዚህ ስትመጡ እኛም እናንተን ለማገልገል በተቻለን አቅም ሁሉ እንሰራልን ብለዋል፡፡በተቋሙ ባህል መሰረት በቆይታችሁ መልካም ስትሰሩ እናበረታታለን ስታጠፉም እንመክራልን ሲያልፍም እንቆነጥጣልን ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ ማንኛውም ተማሪ ጤናማ የእርስ በእርስ ግንኙነት አንዲኖረው እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ብዙ ኪሎሜትሮችን አቋርጣችሁ እዚህ የተገኛችሁት ሰው ለመሆን ነው፤ እናንተ የወደፊት የሃገር ተረካቢ ናችሁ፤ እርስ በእርሳችሁ የአንድ ዓለማ ተቋዳሽ በመሆናችሁ ብሄር፣ ቋንቋ ወይም ሌላ ነገር ሳይገድባችሁ ተስማምታችሁ ኑሩ ሲሉም ምክትል ፕሬዚዳንቱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የደብረብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ዶ.ር ተጠምቀ መሃሪ የትምህርት ቤት ልምዳቸውንና ያሳለፉትን ውጣ ውረድ ለተማሪዎቹ ባካፈሉበት ወቅት እንደተናገሩት መጣችሁበትን ዓላማ እወቁ፤ አላማችሁ ትምህርትና ትምህርት ብቻ ነው፤ እርስ በእርስ በመነጋገርም የተሸለ ሃሳብ ያነሳውን ሰው ሃሳብ የራስ ሃሳብ አድርጋችሁ በመውሰድ ተጠቀሙበት እንጂ የኔ ሃሳብ ብቻ ይደመጥ በሚል አትከራከሩ፤ በክርክር አሸናፊም ተሸናፊም የለም ብለዋል፡፡ዶ.ር ተጠምቀ መሃሪ አክለውም እናንተ ለመጣችሁበት አካባቢ የሰላምና የትምህርት አምባሳደር በመሆን የደብረብርሃን ነዋሪን ሰላም መጠበቅ አለባችሁ ሲሉም ነው መልእክት ያስተላለፉት፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ተማሪ አበበ በላይ የተማሪዎች ህብረት በተማሪ ጉዳይ ገደብ የለሽ ተሳትፎ በማድረግ ስራዎችን እንደሚሰራ ተናግሮ የህብረቱ መቋቋም ዋናው ዓላማም ተማሪው መብቱን እንዲጠቀም፣ መብቱን እንዲጠይቅ ለተማሪው አፍ ሆኖ እንዲጠይቅ በማድረግ ግዴታቸውን በማይወጡ ተማሪዎች ላይ የተጠያቂነት ስርአት መፍጠር መሆኑን አስገንዝቧል፡፡
ተማሪዎቹ በበኩላቸው ማንም ለማንም ስጋት ሳይሆንና የፖለቲካ ትርፍ የሚፈልጉ ግለሰቦችና ቡድኖች በሚያቀናብሩት ሴራ ተሳትፈን ድንጋይ አንወረውርም፤ የዩኒቨርሲቲውን ህግና ስርአት ጠብቀን የመጣንበትን ዓላማ እናሳካለን ብለዋል፡፡