Notice

የቨርሚ ሻይ ፈሳሽ ማዳበሪያና ኮምፖስት ውጤቶችን ለተጠቃሚዎች በሽያጭ አስረከበ

News

በደብረዘይት፣ ዝዋይና ለገዳዴ በሚገኙ የአበባ እርሻዎች ከፍተኛ ቆሻሻ ይመረት ስለነበርና ይህንንም ለማስወገድ ችግር ስለነበረባቸው የእኛን የፕሮጀክት ንድፍ አስገብተን ስለተቀበሉን በ6 የአበባ እርሻ ልማቶች ላይ በመተግበር ውጤታማ ስራ በመስራቱና በተለይ በ5ቱ የአበባ ልማቶች አመርቂ  ውጤት በመመዝገቡ ቴክኖሎጅውን ማስተላለፍ ችለናል ብለዋል፡፡

ከዚህ በመቀጠልም ከቀድምው የሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት በአጣዬና በዩኒቨርሲቲው ግቢ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን በመስራት በተለይ በአጣዬ ከተማ ለሚገኙ 6 ወጣቶች ቴክኖሎጅው ተላልፎላቸዋል፡፡ቴክኖሎጅው ቆሻሻዎችን ወደ ጠቃሚ ማዳበሪያነት በመቀየር ለአሳ፣ለዶሮ፣ለአትክልቶች ምግብነት ስለሚጠቅም ውጤታማ ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ባዩ ቴክኖሎጅ ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር በምዕራብ የሀገራችን ቡና አምራች አካባቢዎች የቡና ገለፈትን ለማስወገድ የሚያስችል ፕሮጀክት ይርጋለም እና አካባቢው ተዋውቋል ያሉት ተመራማሪው ቴክኖሎጅው ውጤታማ በመሆኑና ከዚህ ፕሮጀክት በተረፈው ገንዘብ ኮቱ ላይ ተመሳሳይ ስራ መስራት ተችሏል፡፡ ፕሮጀክቱ ቀጣይነት እንዲኖረው በ(Bio-initiative Africa-BIA/ ድጋፍ በኬንያ ናይሮቢም እየተተገበረ ይገኛል፡፡በይርጋለም ፕሮጀክት 20 ስራአጥ ወጣቶች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

የኮቱ ፕሮጀክት የተጀመረው የቡና ገለፈትን ለማስወገድ የተሰራው ስራ ውጤታማ በመሆኑ ከፍተኛ ገንዘብ ተርፎን ስለነበር ይህንን ገንዘብ እዚህ ቦታ ላይ እንድንጠቀምበት አስፈቅደን 13 ልጆች ተደራጅተው ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ ወጣቶች በኮምፖስት በአሳ፣ በዶሮችና አትክልት ልማት ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡

በዛሬው ዕለት ከአንድነት ፖርክ ጋር የገበያ ትስስር ተፈጥሮላቸው የመጀመሪያውን የተፈጥሮ ማዳበሪያ በፈሳሽና ጠጠር መልክ ለገበያ አቅርበዋል፡፡ ፈሳሽ ማዳበሪያው (Vermy Tea) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ማዳበሪያው ተክሎችን ለማሳደግ፣ ቅጠሉን ለማሳመር እንዲሁም በቅጠሎች ላይ የሚገኙ ተህዋስያንን በማጥፋት ጠቀሜታ እንዳለው ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡በዚህም 250 ሊትር ፈሳሽ ማዳበሪያን 7 ኩንታል ጠጣር የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማቅረባቸውን አስታውቋዋል፡፡

ዶ/ር ገዛኸኝ ደግፌ እንዳሉት የቆሻሻ እጥረት እንደ ተግዳሮት በማጋጠሙ የአንድነት ፖርክ የጠየቀውን ያህል ማቅረብ ባይቻልም በቀጣይ ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ቆሻሻዎችን ወደዚህ ቦታ በማምጣት ለማምረት የሚቻልበት መንገድ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

እንደ ዶ/ሩ ገለፃ ይህ ፕሮጀክት በምስራቅ አፍሪካ በባዮ ኢኒሸቲቭ አፍሪካ /BIA/ የገንዘብ ድጋፍ ይተገበራል፡፡ በቀጣይም በሲያደብርና ዋዩ፣ በአዲስ አበባ አትክትል ተራ፣አልዩ አምባ፣ምንታምር በአዲስ የሚጀሩ ፕሮጀክቶች ሲሆን በደብረዘይትና ይርጋለም አካባቢዎች ደግሞ ፈሳሽ ማዳበሪያ ለማምረት በስፉት ይሰራል ብለዋል፡፡