Notice

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ 2ኛ ቀን ፈተና በሰላም እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ

News

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ 2ኛ ቀን ፈተና በሰላም እየተሰጠ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ ገለጹ፡፡ፕሬዚዳንቱ እንደገለጹት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በዋናው ግቢና በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በጥሩ ስነ-ምግባር እየተሰጠ እንደሆነና ተፈታኝ ተማሪዎችም በተረጋጋ መንፈስ፣በፈተናቸው ላይ በማተኮር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ተማሪዎቹ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ወላጆችና የትምህርት ማህበረሰብ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡
ዶ/ር ንጉስ ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በሰላምና በጥሩ ስነ-ምግባር ፈተናቸውን አጠናቀው እስከሚወጡ ድረስ እንደ ወላጅ ኃለፊነት ወስደን እየሰራን ስለሆነ ወላጆች ከአሉባልታና ተጨባጭ ካለሆኑ ውዥንብሮች እንዲቆጠቡና መረጃዎችን ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶችና ከዩኒቨርሲቲው ህጋዊ ፌስ ቡክ ገጽ ወይም በቀጥታ መጠየቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
ደብዩ
26/11/2015  
Debre Berhan University announces the second day of the 12th grade Natural Science National exam is carried out peacefully.
==========================================================================================================
The president of the University, Nigus Tadese (PhD), said that the second day of the 12th grade Natural Science National exam in DebreBerhan University is being given peacefully. He said that they are working in a calm spirit, focusing on their exams. The president added that the parents and the educational community, who contributed to the students taking their exams calmly, deserve thanks.
In his message, Nigus Tadese (PhD),said that the University is taking responsibility as parents until students complete their exams in peace and good manners, so parents should avoid rumors and confusion. And they can ask for information from the district education offices and the University's official Facebook page or directly.
DBU, 26/11/2015