Announcement - Next

 

ለደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሰራተኞች በሙሉ

ድንበር የለሹ ዘር፣ሃይማኖትና ጾታ የማይለየው የኮሮና ቫይረስን መከላከል የሁሉም ዜጋ ግዴታ ነው፡፡በዓለም ብሎም በሀገራችንና በዩኒቨርሲቲያችን ስጋት ከሆነው የኮሮና ቫይረስ ራስን ነጻ ለማድረግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ተማሪዎች የቫይረሱን ምልክቶችና መከላከያ መንገዶቹን ጠንቅቀው በማወቅ እራሳቸውን እንዲከላከሉ አሳስቧል፡፡በመሆኑም ተማሪዎች በዶርማቸው ሆነው ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዲቻል ዩኒቨርሲቲው እያሳሰበ ከሰኞ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ጀምሮ፡-

1. ማንኛውም ተማሪ ለማንኛውም አይነት አገልግሎት ከግቢ መውጣትም ሆነ መግባት የማይችል መሆኑን፣
2. የነን ካፌ ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ባሉት ሶስቱ የተማሪ ካፊቴሪያዎች እንዲመገቡ የተመቻቸ መሆኑን፣
3. ከአሁን በፊት ከግቢው ለተግባር ልምምድ የወጡ ተማሪዎች በተመደቡበት ቦታ እየሰሩ እንዲጠብቁ፣
4. በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ቤተሰብ የሄዱ ተማሪዎች ወደ ግቢ መግባት እንደማይችሉና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጥንቃቄ እያደረጉ እንዲቆዩ፣
5. ተማሪዎች ወደ ዋናው ምግብ ቤት ሲገቡም ሆነ ሲመገቡም ሳይተፋፈጉ /በቡድን ሳይሆኑ በተናጠል/ ተገቢውን ርቀት ጠብቀው እንዲስተናገዱ እያሳሰብን የመመገቢያ የሰዓት ፕሮግራም በየኮሌጆቻቸው ሊወጣ የሚችል መሆኑን፣
6. የጋራ መጠቀሚያ በሆኑት ፑል ቤቶች፣ዲ.ኤስ.ቲቪ /DSTV/፣ካፍቴሪያዎች ላይ በቡድን ሆኖ መቀመጥና መጠቀም የማይቻል መሆኑን፣
7. የተማሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲባል ሁሉም መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች መግባት አይችሉም፡፡ሆኖም ለስራው የሚያስፈልጉ የዩኒቨርሲቲው የምግብ ቤት ሰራተኞች፣ ፕሮክተሮች ፣ የፀጥታ አካላት፣ ከትምህርት ክፍል በላይ ያሉ የአካዳሚክ ኃላፊዎች/ዲኖችና ተባባሪ ዲኖች/፣ንዑስ የስራ ሂደት መሪዎችና ዳይሬክተሮች፣ ሁሉም ሹፌሮች፣የውሃና የመብራት ጥገና ሰራተኞች፣የክሊኒክ ሰራተኞች፣የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች መምህራን፣የአመራር ጸሐፊዎች፣ሁሉም የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ሰራተኞች ከበር ላይ እጃቸውን እየታጠቡ እንዲገቡ የተወሰነ መሆኑን፣
እያሳወቀን ሰራተኞችና ተማሪዎች ቫይረሱን ለመከላከል የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችን እንዲወስዱ ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ኮሮና ቫይረስን በመከላከል የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ!!

 

 

 

ለሁሉም የደ/ብ/ዩ ተማሪዎች ህብረት  የ2012ዓ.ም አዲስ የፓርላማ አባላት በሙሉ

ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው በሳይንስ እና በከፍ/ት/ምኒስቴር 003/2012 ባወጣው መመሪያ መሰረት ለተማሪዎች ህብረት ዋና ስራ አስፈጻሚነት መወዳደር ለምትፈልጉ ማለትም በቀን 05/07/2012ዓ.ም በነበረው 7ኛ ዙር 17ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በተደረገው ገለፃ መሰረት ምዝገባው ከ09/07/2012ዓ.ም-11/07/2012ዓ.ም ከጠዋት2፡00-ምሽት11፡30 የምንመዘግብ ስለሆነ መወዳደር የምትፈልጉ ሁላችሁም አዲስ የፓርላማ አባላት በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በተማሪዎች ህብረት ቢሮ ማመልከቻችሁን በአካል በመገኘት እንድታሰገቡ ስንል እናሳስባለን፡፡

                                                     የተ/ህ አስመራጭ ኮሚቴ

ማሳሰቢያ፡-

  1. ማንኛውም አመልካች ለመመዝገብ ሲመጣ ማመልከቻው (ስም፣ዲፓርትመንት፣አይዲ፣ስልክ፣ብሎክ፤ዶርም፣ሴክሽን፣ፆታ፣ውጤትና ፊርማ) ማሟላት አለበት፡፡
  2. ማንኛውም አመልካች ለመመዝገብ ሲመጣ የራሱን አይዲ ይዞ መምጣት አለበት፡፡
  3. ከተገለጸው ቀን እና ሰዓት ዘግይቶ ወይም ቀድሞ የሚመጣን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  4. ተወዳዳሪዎች ግዴታ የፓርላማ አባል መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ውድድሩ ተመራቂ ተማሪዎችን አያሳትፍም፡፡

 

ለበለጠ መረጃ፡-

 

https://t.me/DBUstudent

 

+251118903968

 

 

 

 

CONTACT US

Communications Affairs Directorate 

Tel: +251116816286

Fax- 0116812065

Po.Box: 445

FPR@dbu.edu.et

Nigus Tadese (PhD)

DBU President

JoomShaper