1. የሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት፣ ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች
1.1. ተግባርና ኃላፊነት
- በዩኒቨርሲቲው በስርአተ ፆታ ጉዳይ ዙሪያ የሚታየውን የግንዛቤ ችግር መቅረፍ
- ወደ ተቋሙ የሚገቡትን ሴት ተማሪዎች በማብቃት ውጤታማ እዲሆኑ ማገዝ/ማበረታታት
- በተቋሙ ውስጥ የፆታ እኩልነት እንዲሰፍን/እንዲኖር ክፍሉ የበኩሉን ሚና መወጣት
- ሁሉም የተቋሙ የስራ ክፍሎች በእቅዳቸው/በስራቸው/ ውስጥ የስርዓተ ፆታ ጉዳይን አካተው እንዲሰሩ ማስገንዘብ/መከታተል
- በተቋሙ በሚወጡ ልዩ ልዩ መመሪያዎች የፆታን እኩልነት/ የስርዓተ ፆታ ጉዳይ እንዲካተት ማድረግ
- ሴት መምህራንና ሠራተኞች ወደ አመራርነት እንዲመጡ አቅማቸውን ማጎልበት/ማበረታታት/
- ሴቶች የራሳቸውን መብትና ጥቅሞች እንዲያስከብሩ በተለያየ ማህበራትና አደረጃጀቶች እንዲሳተፉ ማድረግ/እንዲደራጁ ማመቻቸት/ማስተባበር/
1.2. ራዕይ
በ2012 ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ለሴቶች ትኩረት በመስጠት ግንባር ቀደም እና ፆታዊ እኩልነት የሰፈነበት ተቋም ሆኖ ማየት፡፡
1.3. ተልዕኮ
- በትምህርታቸው ብቁና ተወዳዳሪ ሴቶችን ማፍራት፣
- በተለያየ ምክንያቶች ትምህርት የሚያቋርጡ ሴት ተማሪዎች ቁጥር እንዲቀንስ የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣
- የስርዓተ ጾታ ጉዳይ ስርፀት እንዲኖር ለሁሉም አካላት የስራቸው አካል አድርገው እንዲሰሩ ማድረግ፣
- በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ሴት ተማሪዎች እና ሴት ሠራተኞች ውሣኔ ሰጭነትና ኃላፊነት መወጣት ማስቻል፣
- በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ሴቶች መረጃ እንዲያገኙ ማድረግና ራሳቸውን ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳ መከላከል እንዲችሉ ማስቻል ፣
1.4. እሴቶች
- ጥራት ያለው አገልግሎት
- ሚስጢር ጠባቂነት
- እኩልነት
- የቡድን ስራ
- ለተገልጋዮች ተገቢውን ክብር መስጠት
መሪ ቃል
“የፆታ እኩልነት ለትምህርት ልማት”