Announcement

ቀን፡ 27/03/2013ዓ.ም

የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ

ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ2012 ዓ. ም ሁለተኛው መንፈቅ አመት የመማር ማስተማር ሂደት ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የተቋረጠዉን ትምህርት ለማስቀጠል፣

  1. በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበራችሁ ተማሪዎች ታህሳስ 1 እና  2/2013 ዓ.ም
  2. ከተመራቂ ተማሪዎች ውጪ ያላችሁ ነባር ተማሪዎች

በሙሉ ታህሳስ 8 እና 9/2013 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትጀምሩ እየገለፅን በጉዞ ላይም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እና ጤና ሚኒሰቴር ያወጡትን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ መመሪያን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ስለሆነ አስፈላጊዉን የመከላከያ መንገዶች ዝግጅት አድርጋችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ

 

 

 

 

ቀን፡ ህዳር 4 2013ዓ.ም

ክፍትየስራቦታማስታወቂያ
 
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን እና ዩኒቨርስቲዉን በምክትል ፕሬዚደንትነት ለመምራት ፍላጎትና ብቃት ያላቸውን iየዩኒቨርስቲውን አካዳሚክ ሰራተኞች አወዳድሮ የላቀ ውጤት ያመጣውን/ያመጣችውን ተወዳዳሪ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መሰየም ይፈልጋል፡፡
1. የስራው መደብ
1.1. የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚደንት፡-ማንኛውንም የምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ነክ ስራዎችን በሃላፊነት ይሰራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል
2. የማመልከቻ መስፈርቶች
2.1. የትምህርት ደረጃ፡- ሶስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) ወይም ተመጣጣኝ፣ ወይም ሁለተኛ ዲግሪ (ኤም.ኤ/ኤም.ኤስ.ሲ) እና ቢያንስ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማእረግ ያለው/ያላት
ማሳስቢያ፡ ሴት ተወዳዳሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ (ኤም.ኤ/ኤም.ኤስ.ሲ) እና በሌክቸረር ማእረግ ማመልከት ይችላሉ
2.2. የስራ ልምድ፡- በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወይም ከዚህ ውጭ ባለ መስክ ለሥራ መደቡ አግባብነት ባለው የተረጋገጠ የአመራርነት/የሃላፊነት እንዲሁም የምርምርና የማስተማር ልምድ ያለው/ያላት
2.3. አጭር ፕሮፖዛል ማቅረብ፡- አመልካቾች የምርምር፣ የማህበረሰብ አገልግሎት፣ የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራትን ለማሳደግና ለማሻሻል ስለሚከተሉት ስልት ከ5 ገፅ ያልበለጠ አጭር መግለጫ/ፕሮፖዛል በፅሑፍ ያቀርባሉ፡፡ አመልካቾች የሚያቀርቡትን አጭር ፕሮፖዛል በእንግሊዘኛ ቋንቋበ”Times New Roman” እና መጠኑ 12 በሆነ ፊደልና የመስመር ስፋት 1.15 ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የፕሮፖዛሉ ኤሌክትሮኒክ ኮፒ በኢ-ሜይል መላክ አለበት፡፡
2.4. ፆታ፡- ማስታወቂያው ሴቶችንና ወንዶችን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ሴቶች ግን እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡
3. ተፈላጊ ከህሎቶች
3.1. የአመራር ክህሎት፡- አመልካቾች በሚወዳደሩበት ስራ ክፍል ያለውን የሰው ሀይል፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ሃብት በማስተባበር ለመምራት የሚያስችል የአመራርነት ክህሎት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3.2. አዲስ አሰራር የመፍጠርና ለውጥ የማምጣት ክህሎት፡- አመልካቾች በሚወዳደሩበት ስራ ክፍል ለውጥና እድገትን ለማምጣት የሚያስችሉ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችን የመቀየስ፣የማመንጨትና ተግባራዊ የማድረግ አቅም ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3.3. የተግባቦትክህሎት፡- አመልካቾች የስራ ዘርፋቸውንም ሆነ የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል የተግባቦትና ከሌሎች ጋር አብሮ የመስራት ክህሎት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
4. ተፈላጊ ስነምግባሮች
4.1. አመልካቾች ከስነምግባር ጉድለቶች የፀዱ፣ በመልካም ባህሪያቸው፣ በስራ አክባሪነታቸውና ታታሪነታቸው የተመሰከረላቸውና ለሌሎች አርአያ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
4.2. አመልካቾች ተግባብተው መስራት የሚችሉ፣ ከአድሎ የፀዱና ሁሉን በእኩል የሚያስተናግዱ፣ ለሚቀርቡላቸው ጉዳዮች ተገቢውን ምላሽ በተገቢው ጊዜ የሚሰጡ መሆን አለባቸው፡፡
5. የስራ ዘመን
በውድድሩ የላቀ ውጤት በማምጣት የተመረጠው/የተመረጠችው አመልካች በምክትል ፕሬዚዳንትነት ለአራት ዓመታት የሚሾም/የምትሾም ሲሆን በመጀመሪያው የአገልግሎት ዘመን በሚያሳየው/በምታሳየው ውጤት ላይ ተመስርቶ የአገልግሎት ዘመኑ/ኗ ለአንድ ተጨማሪ ዙር ሊራዘም ይችላል፡፡
6. ደመወዝና ጥቅማጥቅም
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የደመወዝ ደረጃና ተያያዥነት ባላቸው ህግና ደንብ መሰረት፡፡
7. የማመልከቻ ጊዜ
አመልካቾች ማመልከቻቸውን፤CV፣ የትምህርት፣ የስራ ልምድ እና ሌሎች ማስረጃዎችን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶኮፒ፤ ህጋዊ የመታወቂያ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም አጭር ፕሮፖዛል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የስራቀናት ውስጥ (ማለትም ከህዳር 4 እስከ 17/ 2013ዓ.ም) በስራሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. የማመልከቻ ቦታ
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የስራአመራር ቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ (ከፕሬዚዳንት ፅ/ቤት አጠገብ)
9. የማመልከቻ ማቅረቢያ መንገዶች
አመልካቾች ማመልከቻቸውን በአካል ቀርበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የፕሮፖዛላቸውን ኤሌክትሮኒክ ኮፒ በሚከተሉት የኢ-ሜይል አድራሻዎች መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. and This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
10. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጠቃሚ አድራሻዎች
        የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲድረ-ገፅ፡ www.dbu.edu.et
        ኢ-ሜይል፡ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.    and   This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
        ስልክ ቁጥር፡ 0955346602 ወይም 0913024132
 
 
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ስራአመራር ቦርድ

 

JoomShaper