ጥቅምት29/2017ዓ.ም፡፡ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ
የምህንድስና ኮሌጅ በ2016ዓ.ም በስሩ ካሉት ዲፓርትመንቶች ጋር በመነጋገር ለሀያ ዘጠኝ መመምህራን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎችና ሪልስቴቶች
ከአራት ወር እስከ አንድ አመት ልምድ እንዲያገኙ በማድረግ ያገኙትን እውቀትና ልምድ ለዩኒቨርሲቲው መምህራንና ማህበረሰብ እንዲያካፍሉ
ተደረገ፡፡
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ
ንግግር ያደረጉት የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር)
እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በአዲሱ ልየታ የተግባር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ስለተመደበ መምህራን እውቀታቸውን በተግባር የተደገፈ
መሆን ስላለበት ይህን ተግባር ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ስጥቶ የሚሰራበት በመሆኑ ሁሉም ሊገነዘበውና ሊያውቀው የሚገባ ስራ ነው ሲሉ
ተናግረዋል፡፡መምህራን በኢንዱስትሪዎችና ሪልስቴቶች የሚያደርጉት የስራ
ላይ ልምምድ የዩኒቨርሲቲውንና የአጋር አካላትን ግንኙነት ከማጠናከሩ
ባሻገር ችግሮችን የመፍቻ መንገድ መሆኑን ፕሬዚደንቱ ገልጸዋልዋል፡፡
በመድረኩ ፕሮግራሙን ያስተባበሩት የዩኒቨርሲቲው
የምህንድስና ኮሌጂ ዲን አቶ ተክለፃዲቅ ሽወርቄ እንደተናገሩት የደብረብርሃን
ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ ልየታ የተግባር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ከተለየ በኋላ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ከዚህም ጋር በተያያዘ መምህራን
የተግባር እውቀት ማገኘት ስላለባቸው ከተለያዩ ካምፓኒዎች ጋር እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ አክለውም የዛሬው ፕሮግራም አላማ መምህራን
በሄዱበት የአራት ወር፣ የስድስት ወርና የአንድ አመት በተግባር ላይ የስራ ልምምዳቸው ወቅት ያገኙትን እውቀት ለመምህራንና ለዩኒቨርሲቲው
ማህበረሰብ ማካፈል፣ እንዲሁም በካምፓኒው ሲሰሩ የገጠማቸውን ችግር እንዴት እንደፈቱት ማሳየት ነው በማለት ሀሳባቸውን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው መምህራን በሄዱበት ካምፓኒ ለገጠሟቸው ችግሮች የሚሰጧቸው መፍትሔዎች ካምፓኒውና ዩኒቨርሲቲው የጠነከረ
ግንኙነት እንዲኖራቸው እንደሚያግዝና በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ይህንን ልምድ አጠናክሮ ቢቀጥልና በዚህ ስራ ላይ ያሉ መምህራንን ቢያግዝ
እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብረው ለመስራት የተፈራረሙ ካምፓኒዎች በራቸውን ክፍት ቢያደርጉና እነሱም ወደኛ እኛ ወደነሱ የምንሔድበት
እድል ቢመቻች መልካም ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩም በስራ ላይ የተግባር ልምምዳቸውን
ያደረጉ መምህራን የሔዱበትን ቦታና የሰሩትን ስራ አቅርበዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ከኤሌክትሪካል ትምህርት ክፍል መምህር አትንኩት ባዩ ፌቤላ የኤሌክትሪክ መኪኖች መገጣጠሚያ ካምፓኒ፣ ከመካኒካል
ትምህርት ክፍል መምህር ስንታየሁ አሰፋ ቢጃይ ኢትዮጵያ፣ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ትምህርት ከፍል ዮአዳን ሙሰማ አሚባራ ሪልስቴት፣ ከምግብ ኢንጅነሪንግ መምህር መላክ
ሙጨ ኤልፎራ አግሮ ፕሮሰስ ኢንዱስትሪ ኮምቦልቻ ቄራና ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እና በተመሳሳይ ሌሎች መምህራን በየድፓርትመንታቸው በመሰባሰብ ያገኙትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የገጠሟቸውን
ችግሮች አቅርበዋል፡፡