ደብረ ብርሃን
ዩኒቨርሲቲ
ለደብረ
ብርሃንና
አካባቢው
የኢንዱስትሪ
ከፍተኛና
መካከለኛ
አመራሮችና
ባለሀብቶች
የአመራርነት
የአቅም
ግንባታ
ስልጠና
ሰጠ።
ህዳር
05/2017 ዓ.ም
በዩኒቨርሲቲው
የኢንዱስትሪ
ትስስር ዳይሬክቶሬት
በተዘጋጀው
በዚህ
ስልጠና
የኢንዱስትሪ
ከፍተኛና
መካከለኛ
አመራሮች፣
ባለሀብቶችና
ሙያተኞች
ተገኝተዋል።
ካሳሁን በቀለ
(ዶ/ር)
የምርምርና
ቴክኖሎጂ
ሽግግር
ም/ፕሬዚዳንት
ተወካይ
ዩኒቨርሲቲው
ለኢንዱስትሪ
አመራሮችና
ሙያተኞች
የአቅም
ግንባታ
ስልጠና
እያዘጋጀ አቅማቸውን
ማሳደግ
ይፈልጋል
ብለዋል።
ዛሬ
ከአመራሩ
ይጀመር
እንጂ
ቀጣይነት
ባለው
መልኩ
ተጠናክሮ
ይቀጥላልም
ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው
ከኢንዱስትሪዎች
ጋር
ለመስራት
አዳዲስ
ስራዎችን
ጀምሯል
ያሉት
ተወካዩ
በቅድሚያ
አምራች
ኢንዱስትሪዎች
ችግሮቻቸው
ምንድነው
በሚል
የመለየት
ስራ
እየተሰራ
እንደሚገኝም
ተናግረዋል። አክለውም
በምርምርና
በቴክኖሎጂ
ሽግግር
በጋራ
ለመስራት
እንደዚህ
አይነት
መድረክ
ጠቀሜታው
የጎላ
እንደሆነም
ገልጸዋል።
በመጨረሻም ቀጣይ
በምን
እንደግፋችሁ
የሚል
ጥያቄ
ካነሱ
በኋላም
ዩኒቨርሲቲው
ያሉትን
ቴክኖሎጂዎች
የመፈተሽ፣
ተማሪዎችን
የማብቃትና
የማሰልጠን
እንዲሁም
በማስተማር
እውቀት
ማካፈል
እንደሚችሉ
ተናግረዋል።
ትምህርታቸውን
ማሻሻል
እንደሚችሉና
ለዚህ
ደግሞ
የተቀመጡ
የአሰራር
መመሪያዎች
መኖራቸውን
ገልጸው
ተማሪዎቻችንን
ብቻ
ተቀበሉ
ማለት
አግባብነት
የለውም
ብለዋል።
በደብረ ብርሃን
ዩኒቨርሲቲ
የኢንዱስትሪ
ትስስርና
ቴክኖሎጂ
ሽግግር
ዳይሬክተር
ሰለሞን
ደርቤ
ስልጠናው
በዋናነት
ለተለያዩ
ከፍተኛና
መካከለኛ
አመራሮች
የተዘጋጀ
የአቅም
መገንቢያ
ስልጠና
መሆኑን
ገልጸው
ከ40
ለሚልቁ
ኢንዱስትሪዎች
ጥሪ
ተላልፏል
ብለዋል።
የዛሬው
ግንኙነታችን
ሁለት
ዓላማ
አለው
ያሉ
ሲሆን
የአመራርነት
ክፍተትን
መሙላትና
በቀጣይ
በሚኖራቸው የምርምር፣
የማማከር
፣
የስልጠና
ፍላጎትና
የቴክኖሎጂ
ሽግግር
ስራዎች
ዙሪያ
ከአመራሩ
ጋር በመነጋገር
በጋራ
ለማቀድ
እንደሆነም
ተናግረዋል።
ከአሁን በፊት
በዩኒቨርሲቲው
ለአነስተኛና
ጥቃቅን
ኢንዱስትሪዎች
የተላለፉ
5 የቴክኖሎጂ
ውጤቶች
መኖራቸውን
የጠቀሱት
ሰለሞን
ደርቤ
አዳዲስና
ተጨማሪ
የቴክኖሎጂና
የምርምር
ስራዎች
በሂደት
ላይ
እንዳሉ
ተናግረዋል።
በዋናነት
በቴክኖሎጂ
ሽግግር፣
በማማከርና
በስልጠና
ስራዎችን
እየሰሩ
እንደሚገኙም
ገልጸዋል።
ከኢታል አሉምኒየም
ማንፋክቸሪንግ
ፒ
ኤል
ሲ
የመጡት
ተፈራ
ሰይፉ
በዩኒቨርሲቲው በተደረገላቸው
ጥሪ
መሠረት
ስልጠናው
ላይ
እንደተገኙ
ገልጸው
ስልጠናዎች
በየጊዜው ቢዘጋጁ
አዳዲስ
እውቀቶችን
ለመቅሰምና
ራስን
ከዘመኑ
ጋር
እኩል
ለማስኬድ
እድል
ይፈጥራል
ብለዋል።
የዛሬው
ስልጠና
እስካሁን
ባለኝ
ልምድና
የስልጠና
እውቀት
ብዙ
አለማወቄን
የተገነዘብኩበት
ነው
ሲሉም
ገልጸዋል።
አቶ
ተፈራ
ሰይፉ ስልጠናዎች
የሰራተኛውን
መብትና
ጥቅም
በማስከበር፣
የድርጅቱን
ስምና
አገልግሎት
ጠብቆ
ዘላቂ
በማድረግ፣
በአጠቃላይ
ሰራተኛው፣
የድርጅቱ
ባለቤቶች፣
ህብረተሰቡና
ሀገር
ለላቀ
ጥቅም
እንዲነሳሱ
ፋይዳው
የጎላ
መሆኑን
አክለው
ተናግረዋል።
ከዩኒቨርሲቲው
ጋር
ያላቸውን
ትስስር
ሲገልጹም ድርጅታቸው
ለህብረተሰቡ
የተቋቋመ
በመሆኑ
ተማሪዎች
ተመርቀው
ሲወጡ
ባለው
ክፍት
ቦታ
ውስን
በሆነ
መልኩ
የስራ
እድል
እየፈጠረላቸው
እንደሚገኝ
ገልጸዋል።
ድርጅታቸው
በፕሮግራም
የተደገፈ
የተማሪዎች
የልምምድ
ጊዜ
እንዳለውና
በልኩ
ዩኒቨርሲቲው
የሚልካቸውን
ተማሪዎች
ተቀብሎ
የሚያስተናግድበት አሰራር
እንዳለው
ተናግረዋል።
አሁን
በተያዘው
አግባብና
በሌሎችም
ጉዳዮች
ዙሪያ
ወደፊት
በይበልጥ
ተቀራርበን
ልንሰራ
ይገባል
በማለት
አቶ
ተፈራ
ሰይፉ
ሀሳባቸውን
ሰጥተዋል
።