Notice

በሰላማዊ መማር ማስተማር ዙሪያ ምክክር አደረገ

News

 የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከዞን፣ከከተማ አመራሮች፣ከሁሉምቀበሌ አመራሮች፣የሀገርሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣ታዋቂ ግለሰቦች፣የእድር መሪዎች፣የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች፣የትምህርት ተቋማት አመራሮችና ምሁራን በተገኙበት በሰላማዊ መማር ማስተማር ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡

የምክክር መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኃይለማርያም ብርቄ ሀገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴውን ለመቀልበስ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመጠቀም የሚሞክሩ ሀይሎች በመኖራቸው ይህ መድረክ የእነዚህን ኃይሎች እንቅስቃሴ ለመቀልበስና ሰላማችንን ለማስቀጠል የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡እንደ ፕሬዚዳንቱ ዩኒቨርሲቲው አሁን ያለውን ሰላም ለማስቀጠል የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ይህ መድረክ የበለጠ ሊያጠንክረው ይችላል ብለዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን አዴፓ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ገብረጻዲቅ በበኩላቸው የሰላምን ጠቀሜታ የምናውቀው ሰላማችን ሲደፈርስ ብቻ ነው፡፡ “ሰላምን ከገንዘብ ውሃን ከቀለብ የሚቆጥረው የለም::” ስለሆነም ሰላማችንን እንደ ገንዘብ በመቁጠር ልናስጠብቅና ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ ከፌደራል ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የውይይት መነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡በመድረኩ የዩኒቨርሲተውን ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ ይሰራል በማለት ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡

በመጨረሻም በሰላም ማስጠበቅ ዙሪያ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡