Notice
በዓሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ28ኛ ጊዜ፣በሀገራችን ለ13ኛ ጊዜ በክልላችን ለ9ኛ ጊዜ፣በዩኒቨርሲቲው ለ8ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የዩኒቨርሲቲውን የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት መልዕክት አቅርበዋል፡፡በመልዕክታቸውም ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ መማር ማስተማሩን ለማሳለጥ ጾታዊ ጥቃትን የማይደራደር ማህበረሰብና ተማሪ ለመፍጠር ተግተው እንደሚሰሩ አስታውቀወል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮምሽን ጾታዊ ጥቃት ከሰብዓዊ መብቶች ጋር ያለውን ተዛማጅነት አስመልክቶና ወደፊት ምን እንደሚጠበቅ የሚያወሳ ዳሰሳዊ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በተሳታፊዎችም አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው የፌደራል ሰብዓዊ መብት ኮምሽን የሴቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትሁን ሽፈራው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡