Notice

በተማሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በእርቅ ሰላም ተቋጨ

News

እየደረሰባቸው ነው በሚል ተቃውሟችንን በሰልፍ መግለጽ አለብን በማለት ተቃውሞ ለማንሳት ባደረጉት ሂደት በአማራና በኦሮሞ ብሔር ተማሪዎች መካከል አለመግባባት ፈጥሯል፡፡

የተፈጠረውን አለመግባባት የሐይማኖት አባቶች፣የሐገር ሽማግሌዎች፣የጸጥታ አካላትና የሁለቱ ብሔር ተወካዮች ከተማሪዎቹ ጋር በተከታታይ ባደረጉት ውይይት እርቅ የወረደ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም በሂደቱ በተወሰኑ የተማሪዎች መኝታ ክፍሎች፣ቤተ-መጻህፍትና ምግብ ቤቶች መስኮቶች ላይ የመሰባበር መጠነኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኃይለማርያም ብርቄ ለተማሪዎቹ ችግሮቻቻውን በሰለጠነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማቅረብ እንዳለባቸውና የማንም የከሰረ ፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያና የግል ጥቅም ማስከበሪያ ወኪሎች እንዳይሆኑ አሳስበዋል፡፡‹‹እናንተ የኢትዮጵያ ታሪክ ሰሪዎች እንጂ ታሪክ አፍራሽ አይደላችሁም›› ሲሉም ነው የገለጹት፡፡ፕሬዘዳንቱ አክለውም የግል ጥቅምን መሰረት በማድረግ ወንድም ከወንድም እህት ከእህት በማጣላት በወንድማማቾች መካካል ጠብ ለሚጭሩ አካላት ዩኒቨርሲቲውና የአካባቢው ማህበረሰብ ፈጽሞ የማይታገሳቸው በመሆኑ ከዚህ እኩይ ተግባራችው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡የተፈጠሩ አስተዳደራዊ ችግሮችንም ለማስተካከል ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

የሐይማኖት አባቶቹ ሐይማኖታዊ አስተምህሮ የታከለበት አባታዊ ምክራቸውን በመለገስ ተማሪዎቹ ወደትምህርታቸው እንዲመለሱ ያሳሰቡ ሲሆን ተማሪዎቹ ያነሷቸውን ጥቄዎች ተከታትለው እንደሚያስፈጽሙና ቀጣይነት ያለው ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ተወካይ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ በበኩላቸው የተማሪዎቹ ጥያቄ አግባብነት እንዳለው ተናግረው በኦሮሚያ ክልል ለሚማሩ የአማራ ብሔር ተማሪዎች ከለላና ዋስትና የኦሮሞ ህዝብ እንጂ እዚህ ያለው ተማሪ አይደለም ብለዋል፡፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ችግሮቹ ተፈጠሩ በተባሉባቸው አካባቢዎች ከሐገር ሽማግሌዎችና ከሐይማኖት አባቶች ጋር በመሆን በጎ ስራዎችን አየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚታየውን ግጭት እዚህ መድገሙ ተገቢ እንዳልሆነ ይልቁንም ሌላ ቦታ የሌለውን ሰላም ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በማምጣት ለሌሎቹ ምሳሌ መሆን ይቻላል ብለዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ም/አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ታዬ በበኩላቸው ተማሪዎች የሀገር ተረካቢ እንደመሆናችሁ መጠን በተማሪዎች መካከል ሰላማዊ ግንኙነት ከምንም በላይ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ተማሪዎቹ ባለ 7 ነጥብ የጋራ አቋም መግለጫቸው ተሰምቶ በሐይማኖት አባቶች ፀሎትና ቡራኬ እርቀ ሰላሙ ተቋጭቷል፡፡በአቋም መግለጫዎቻቸውም፡-

1.በሀገራችን በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ላይ በማንነታቸው የሚፈጸሙ ጥቃቶች በአፋጣኝ እንዲቆሙ እንጠይቃለን፡፡

2.በዩኒቨርሲቲያችን ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እናወግዛለን ለመንግስትም አጋልጠን እንሰጣልን፡፡

3.ዩኒቨርሲቲያችን የምርምርና የቴክኖሎጅ መፍጠሪያ ማዕከል፣የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነትና የመተባበር ኢትዮጵያዊነት እሴቶችን የምናዳብርበት እንጅ የብጥብጥ ማዕከል እንዲሆን አንፈቅድም፡፡

4.እኛ ተማሪዎች ችግሮች ሲፈጠሩ የመፍትሄ አካል እንጅ የሌሎች አካላት ተፅእኖ ተሸካሚ አይደለንም፡፡

5.በእኛ በተማሪዎች መካከል ሰላማችንን፣ፍቅራችንን፣አንድነታችንንና ኢትዮጵያዊነታችንን የሚሸረሽር ማንኛውም አካል እንዲቆምልን እንጠይቃለን፡፡

6.እኛ ተማሪዎች ትምህርታችንን ጠንክረን በመማር ኢትዮጵያዊ አንድነትን፣እድገትን ሰላምንና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጠንክረን እንሰራለን፡፡

7.ዩኒቨርሲቲዎቻችን ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ነጻ እንዲሆኑ አጥብቀን እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

 

 

/ደብዩ ኮ.ጉ.ዳ፡ታህሳስ 14/2011 ዓ.ም/