Notice

ለዩኒቨርሲቲው የመፅሐፍት ስጦታ ተበረከተ

News

ለቤተመፃህፍትና ዶክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለአቶ ስምኦን ወንድምአገኘሁ ታህሳስ 23/2011 ዓ/ም አስረክበዋል፡፡

ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ የመጀመሪያው የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ “የቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ፡የከፍተኛ ትምህርት መቋቋሚያና መስፋፋት ጉዞ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተጻፈ 630 ገፆች ያሉት 5 መፅሐፍትን እና በኢንጅነር ተረፈ የራስወርቅ የተፃፈ “የአንኮበሩ ሰው በጀኔቫ የኢትዮጵያ የአለም የቴሌኮምኒኬሽን ትረካ” የሚል 10 መጽሐፍትን ለዩኒቨርሲቲው ቤተመፃህፍት እንዲሁም 5 መፅሐፍትን ደግሞ በምርቃት ዝግጅት ላይ ተሳትፎ ላደረጉ ተማሪዎችና መምህራን ማበርከታቸውን  ዶ/ር አልማዝ አፈራ ገልጸዋል፡፡

መጽሐፍቶቹን የተረከቡት የዩኒቨርሲቲው ቤተመፃህፍትና ዶክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስምኦን ወ/አገኘሁ እንደገለጹት መጽሀፍቱ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና መምህራን፣ ለተማራማሪዎች፣ እንዲሁም ለመማር ማስተማር ሄደቱ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ እና የላቀ ልምድና እውቀት እንደሚያስጨብጡ በመግለጽ መጽሐፍቶቹን ጽፈውና አሳትመው ላበረከቱት ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ እና ኢንጅነር ተረፈ የራስወርቅ ምስጋና አቅርበዋል፡፡