Notice
ባካሄደው ውድድር 10 ወርቅ 12 ብር እና 14 ነሀስ በመሰብሰብ አጠናቋል፡፡
የአማራ ክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ እምቢአለ ቦጋለ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት ውድድሩ ወንድማማችነትን፣ ፍቅርን እና ወዳጅነትን በተግባር የሚገለጽበት በመሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ም/ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት የውድድሩ አላማ እትሌቶች ራሳቸውን የሚፈትኑበት፣ ለከፍተኛ ክለቦች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚታጩበት እንዲሁም ክልሉን ወክለው የሚሳተፉ ምርጥ አትሌቶችን ለመምረጥ እንደሆነ አስረድተው ማንኛውም ተወዳዳሪ ክለብ ወይም አትሌት የተገኘውን ምቹ አጋጣሚ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል፡፡
ከጥር 3 እስከ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም በባህርዳር አለምአቀፍ ስታዲየም በተካሄደው ውድድር ከ8 በላይ ከአትሌቲክስ ክለቦች የተሰባሰቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አትሌቲክስ ክለብ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ በነበሩት ቀናት የአካባቢውን ባህል ልብስ በመልበስና በማስተዋወቅ፣ ውድድሩን በመልካም ስነ-ምግባር በማካሄድ እንዲሁም በአሰልጣኞችና አትሌቶች የተቀናጀ ተግባር የዋንጫ ተሸላሚ እንደሆኑ የክለቡ ስራ አስኪያጅና የዩኒቨርሲቲው የስፖርት ሳይንስ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ አብር ገልጸዋል፡፡