Notice

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ 3064 ተማሪዎችን አስመረቀ

News

ዩኒቨርሲቲው በ2011 ዓ.ም ካስመረቃቸው በመጀመሪያ ድግሪ መደበኛው ፕሮግራም 1389 ወንድ፣ 927 ሴት፡ በድምሩ 2316 ፣ በማታና በተከታታይ ትምህርት 303 ወንድ፣ 293 ሴት በድምሩ 596 ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን በአጠቃላይ በመደበኛ፣ በማታና በተከታታይ መርሃ-ግብሮች 1692 ወንድ፣ 1220 ሴት በድምሩ 2912 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም በ2ኛ ድግሪ መደበኛና  በተከታታይ ፕሮግራም 119 ወንድ 33 ሴት በድምሩ 152 ሰልጣኞች ተመርቀዋል፡፡ በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ድግሪ እና በ2ኛ ድግሪ ፕሮግራሞች 3064 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡