Notice
ሲሰጥ የቆየውን የጋዜጠኝነት ተሰጥኦ ፍለጋ ፕሮጀክት ስልጠና ስልጠና መስከረም 3/2012 ዓ.ም በህዝብ ግንኙነት አዳራሽ የማጠናቀቂያ ፕሮግራሙን አካሂዷል፡፡
በስልጠናው የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የደብረብርሃን ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ይመር እንዳሉት ደብረብርሃን ፋና ኤፍ ኤም 94.0 የተማሪዎችን የጋዜጠኝነት ተሰጥኦ በማውጣት ለሰጡት ተግባራዊ ስልጠና ምስጋናቸውን አቅርበው ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋርም በሌሎች ተሰጥኦዎች ዙሪያ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ጸዳለ ገብረጻዲቅ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን የጋዜጠኝነት ተሰጥኦ ፍለጋ ፕሮጀክት ስልጠና በዩኒቨርሲቲው የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ከፋና ኤፍ ኤም 94.0 የተዘጋጀ እንደሆነ ገልጸው ፕሮጀክቱ የተጀመረበት ምክንያት ሚዲያ የአንድን ሀገር ዲሞክራሲያዊ ህልውና ለመወሰን ትልቅ ሚና ስላለው በፍጥነት እያደጉ ባሉት ማህበራዊ ሚዲያዎች ጭምር ህልውናችን እየተናጋ መሆኑ እሙን ነው፡፡ለዚህም በባለሙያ የሚመራ፣ሙያዊ ፍቅር ያለው ባለሙያና ሚዲያ ስለሚያስፈልገን ይህንን ለማድረግ ደግሞ በህጻናት ላይ መስራት አዋጭ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አቶ ሰለሞን አየለ የደብረብርሃን ፋና ኤፍ ኤም 94.0 ስራ አስኪያጅ በበኩላቸው የተሰጥኦ ፍለጋ ፕሮጀክትን ለማስጀመር ረዘም ያለ ጊዜ ቢፈጅም ስራውን ከኮሌጁ ጋር በጋራ መስራት በመቻላችን ውጤታማ መሆን ችለናል ብለዋል፡፡ስራ አስኪያጁ አያይዘውም ሚዲያ ነጻነት ይፈልጋል፡፡ነጻነት ቢኖርም እውቀትና ክህሎት ያስፈልጋል፡፡ቀጣይዋ ኢትዮጵያ እውቀትና ክህሎት ያለው ባለሙያ ያስፈልጋታል፡፡ይህንን እውን ለማድረግ በልጆችና ህጻናት ላይ መስራት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡እንደ አቶ ሰለሞን ሰልጣኞቹ በተግባር የታገዘ፣ስነምግባራዊና ሞራላዊ ስልጠና አግኝተዋል ብለዋል፡፡በተጨማሪም ፋና ኤፍ ኤም 94.0 በሰልጣኞች የተዘጋጀ የህጻናት ፕሮግራም መጀመሩንም አብስረዋል፡፡
በመጨረሻም ከሰልጣኞች፣ ከሰልጣኝ ቤተሰቦች እና ከክብር እንግዶች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች መልስ በመስጠት፣አስተያየት በመቀበልና የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡