Notice
ሲምፖዚየም አዘጋጀ፡፡ በሀገርና በክልል ደረጃ የሚገኙ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች፣ የዞንና ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ አጋር አካላትና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተሳተፉበት መድረክ እንደነበር ታውቋል፡፡
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አልማዝ አፈራ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም ወቅት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ6500-7000 የሚደርሱ የተለያዩ የእጽዋት ዝርያዎች እንዳሉ እና ከነዚህም ውስጥ 10-12 ፐርሰንት ሀገር በቀል እጽዋቶች መሆናቸውን ጥናቶች ያመላክታሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡ እንደ ዶ/ር አልማዝ ገለጻ በታዳጊ አገሮች 80 ፐርሰንት የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ባህላዊ መድሃኒትን የሚጠቀም ሲሆን ኢትዮጵያም የዚሁ አንዱ አካል ነች ብለዋል፡፡ አክለውም የባህል ህክምናውን ለማዘመን ከባህል መድሃኒት አዋቂዎችና ተመራማሪዎች ጋር ያለው ህጋዊ ቁርኝት ማጠናከር ይገባል
ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአንኮበር መድሃኒታዊ እፅዋት ቅመማና ብዝሀ ህይወት እንክብካቤ ፕሮጀክት ማዕከል የተቋቋመበት አላማ፣ በማዕከሉ የተከናወኑ ስራዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የወደፊት እድሎችን የዳሰሰ ጹሑፍ በፕሮጀክቱ ዳይሬክተር በዶ/ር አማረ አያሌው ቀርቧል፡፡ በመቀጠልም በዶ/ር ኤርሚስ ልኡለቃል “ከመድሃኒታዊ እጽዋት ጠቃሚ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘትና ተያያዥ ተግዳሮቶች ምንድንናቸው”፤ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብና ጤና ኢንስቲቱትና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካይ ዶ/ር አሰፋ ደበላ “የባህል ህክምና አዋቂዎች ለጤናው ዘርፍ ያላቸውን አስተዋፅኦ እና ለማዘመን ያላቸው ሚና” እንዲሁም በሌሎች ርዕሰ ጉዳች ዙሪያ ጥናታዊ ጹሑፎች ቀርበው ጥልቅ ውይይት እንደተካሄደ ለማየት ተችሏል፡፡
የሲምፖዚሙ ተሳታፊ የሆኑት የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ሃጂ ሸክ አሊ አደም እንደገለጹት ቀደም ሲል በባህል መድሃኒት አዋቂዎች እና በምሁራን መካከል ያለመተማመን እንዲሁም በጋራ ያለመስራት ፍላጎት እንደነበር ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ ህብረተሰቡ እና የተማረው አካል ለባህል መድሃኒት አዋቂዎች የሚሰጠው
ግምት በእጅጉ የላቀ መሆኑን ገልጸው በጥናትና ምርምር እንዲታገዝ በቅንጅት በመሰራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
አያይዘውም የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበር በመላ ሀገሪቱ የባህል መድሃኒት አዋቂዎችን በማህበር በማሰባሰብ ከምሁራን ጋር ትስስር በመፍጠር ወደ ዘመናዊ ህክምና እንደሸጋገር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ሌላኛው ተሳታፊ አቶ ኪዳነማሪያም ወ/ማሪያም በኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበር ውስጥ አስተባባሪ ሲሆኑ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ሲምፖዚየም እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊ ነው ብለዋል፡፡ መድረኩም ቀደም ሲል ትኩረት የተነፈገውን የባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎችን ተግባር የሚያድስ ምሁራንና ባለሙያውን በአንድነት ያገናኘ መድረክ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡