Notice

ከ4000 በላይ የእጅ ንፅህና መጠበቂያዎችን እያሰራጨ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ

News

በኬሚስትሪ ቤተ ሙከራውስጥ 3000 ሊትር በላይ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በማዘጋጀት እንዲሁም ከ1000 ሊትር በላይ የተገዛ የንጽህና መጠበቂያ በድምሩ 4000 ሊትር በላይ የእጅ ንጽህና መጠበቂያዎችን ዞኑ ውስጥ ላሉ ሆስፒታሎች ፣ ጤናጣቢያዎች ፣ ለዞን እና ለወረዳ መስሪያ ቤቶች እና ለሀበሻ አረጋዊያን ማዕከል ለመሳሰሉት ተቋማት በማሰራጨት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለጤና ጣቢያዎቹ ለሆስፒታሎች እና ለአረጋዊያ ማዕከሉ ከእጅ ንጽህና መጠበቂያ በተጨማሪ በአንኮበር ምርምር የተገኘውን የመጸዳጃ ቤት ንጽህና መጠበቂያ ፈሳሽ ሳሙና እንዲደርሳቸው እየተደረገ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡ዩኒቨርሲቲው በአምስት ክላስተሮች ለሚገኙ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ማለትም በደብረብረሃን፣ መርሃቤቴ፣ ይፋት፣መንዝና ቡልጋ ክላስተሮች የመጸዳጃ ቤት ማጽጃና ሳኒታይዘር ስርጭት አካሂዷል፡፡
በተያያዘም የዩኒቨርሲቲው የጤና ባለሙያዎች ፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና አመራሮች እየሰሩት ያለው ሥራ እጅግ በጣም አመርቂና በእንዲህ አይነት የችግር ወቅት በርግጥም በጋር በመስራት ችግሩን መመከት እንደሚቻል ጥሩ ማሳያ እንዲሆነ ፕሬዚዳንቱ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ የኮረና ቫይረስ surveillance data base የጤና እና የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ መምህራን በጋራ በመሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችል የመረጃ ቋት በሀገር ደረጃ መኖር ስላለበት Map Based የሆነ የመረጃ ቋት እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው ይህን የመረጃ ቋት ዝግጅት ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ኢንስቲትዮት ፣ ከኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከመረጃ ደህንነት ተቋማት ጋር ለማቀናጅትና ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው የአፍ ፣የአይንና የጆሮ ማፅጃ የሚሆን ሳኒታይዘር በአንኮበር የመድሃኒታዊ ዕፅዋት ምርምር ላይ እየተሳተፉ ያሉ የኬሚስቲሪ ፣ የኬሚካል ኢንጅነሪግ እንዲሁም የሜዲሲን መምህራን በጋራ በመሆን ተስፋ ሰጭ ምርምር በማድረግ ለማዘጋጀት ልዩ ጥናት እያደረጉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡