Notice

ደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብሎ እየሰራ ይገኛል ተባለ

News

እነዚህ ኮሚቴዎች የአካባቢውንና የዞኑን ማህበረሰብ በግንዛቤ ማስጨበጥ፣የquarantine እና Isolation room በማዘጋጀት በገንዘብና በማቴሪያል ድጋፍ፣በሳኒታይዘር ምርትና ስርጭት እንዲሁም የምርምር ስራዎች ላይ እየሰራ መሆኑ ታውቋል፡፡

ዶ/ር ንጉስ ታደሰ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት የኒቨርሲቲው በሀገራችን የተከሰተውን ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላክል የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡ቫይረሱን የመከላከል ሥራን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው በዞንና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር የዩኒቨርሲቲው የጤና እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን በማቀናጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በሞንታርቦ ፣ በበራሪ ወረቀቶች ፣በርካታ በሲዲ የተቀረፁ መልዕክቶችን በማዘጋጀት ለቀበሌዎች ፣ ለወረዳዎች እና ለዞን የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤቶች አባዝቶ በመስጠት፣ፖስተር ፣ ባነርእና LED Screen በማዘጋጀት የግንዛቤ ፈጠራ ሥራውን አስፍቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ፕሬዚዳንቱ አክለውም የለይቶ ማቆያ እና ህክምናን በተመለከተ የ07 ቀበሌ ጠባሴ ጤና ጣቢያ ፣ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ደግሞ 13 ብሎኮችን ጨምሮ ለQuarantine እና Isolation በተሟላ መልኩ ቁሳቁስ በማሟላት ዝግጅት ያደርገ ሲሆን ማንኛውም ተጠርጣሪ ከተገኘ ለይቶ ለማቆየትና ወደ ሚመለከተው ምርመራና ህክምና ለመወሰድ የሚያችል ዝግጅት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን አሳውቀዋል፡፡ለእነዚህ ማቆያና ማከሚያ የሚወል ከ600,000 ብር በላይ በገንዘብና በቁሳቁስ እንዲሁም በዞን ደረጃ ለተቋቋመው አብይ ኮሚቴ ሥራ ማስኬጃና ልዩልዩ ሥራዎች የሚውል 500,000 ብር በድምሩ 1,100,000 ብር በጥሬ ገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ መሆኑ ገልጸዋል፡፡
እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ዩኒቨርሲቲው ደ/ብርሃን ከተማ ላይ የሚገኘውን የሀበሻ አረጋዊያን ማዕከል ከዚህ በፊት ከህብረተሰቡ ድጋፍ የሚያገኙ ከ100 በላይ አረጋዊያን በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲው ሙሉ በሙሉ ተረክቦ ቁርስ ፣ ምሳ እና እራት እየመገበ ሲሆን ለእነዚህ አረጋዊያን የንጽህና መጠበቂያ ሳሙና እና ሳኒታይዘር በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ከዶዶላ ተፈናቅለው ለመጡ ግለሰቦች የፍራሽና የምግብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡