Notice

በአስተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ስር ላሉ ባለሙያዎች እና አመራሮች ስልጠና ሰጠ

News

በስልጠናው ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአሰተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለምነው መልካሙ ስልጠናው እየተሰጠ ያለው በተማሪዎች አገልግሎት ስር ላሉ የስራ ክፍሎች በ3 ዙር ከፍለን ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ለጤና ባለሙያዎች፣ በ2ኛ ዙር  በምግብ ቤት ዙሪያ እና በ3ኛ ዙር ደግሞ ለፕሮክተሮች እና ሌሎች በተማሪዎች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ስልጠናውን ይወስዳሉ በማለት ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም የስልጠናው ዋና አላማ እያንዳንዱ የምግብ ቤት አመራር እና ባለሙያ እንዴት ኮረናን እየተከላከለ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ሲሆን ሃላፊነቱን የማይወጣ አመራርም ሆነ ባለሙያ ከቀላል እስከ ከባድ ቅጣት የሚያሰጥ መሆኑን ለማሳወቅ እና ለማስረዳትም ጭመር ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የደብረብርሃን ዩነቨርሲቲ የህክምና ኮሌጅ መምህር እና በደብረብርሃን ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ሃኪም የሆኑት ዶ/ር መሀመድ አወል ስልጠናው ከዚህ ቀደም የተሰጠ ቢሆንም አሁንም በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሰጠቱ ሰዎች እንዴት እራሳቸውን ከኮረና መከላከል እንደሚችሉና ተማሪዎችን ለመቀበልና ለማስተናገድ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡አያይዘውም በተለይ መስተንግዶ ላይ ያሉ ባለሙያዎች ፊት ለፊት ስላሉ ለተማሪዎችም ሆነ ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ ሲባል ሰርጅካል ማስክ ቢጠቀሙ መልካም ነው ብለዋል፡፡

በስልጠናው ተሳታፊ የነበሩት አቶ አሸብር ሙሉጌታ የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ምግብ ቤት ሃላፊ   ስልጠናው እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ እና በቂ እውቀት እንደጨበጡበት በመናገር በምግብ ቤት ዙሪያ ኮረናን ለመከላከል አስፈላጊ ግብዓቶችን ማለትም ማስከ፣ሳኒታይዘርና ሳሙና እንዲሁም ለቃዎች መዘፍዘፊ በረኪና፣መቀቀያ ቮይለር በተቻለ መጠን እያዘጋጀን ነው ብለዋል፡፡

ሌላው ተሳታፊ የነበሩት አቶ መብሬ ተሾመ በደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ምግብ ቤት የመስተንግዶ ማህበር ሊቀመንበር ስልጠናው ከዚህ ቀደም እንደተሰጣቸው እና አሁንም ግንዛቢያቸውን የበለጠ እንዳዳበረላቸው ገልፀው በሽታውን ለመከላከል ለተማሪዎቻችን አርያ መሆን የምንችለው እኛ ስለሆን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴችን መከላከያ መንገዶችን በተግባር መፈፀም መቻል አለብን በማለት ሃሳባቸውን ተናገረዋል፡፡