Notice
በስነ ሰርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኛችና ተማሪዎች ተገኝተው ያላቸውን ክብርና ድጋፍም ገልጸዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን፣ የአማራ ክልል ልዩ ሀይልና ሚሊሻ አባላት በሰሜኑ የትግራይ ክልል እያካሄዱ ባለው የጸጥታ ማስከበር እርምጃ እና ለፌደራል ስርአቱ አልገዛም ባለው የህወሀት ቡድን በሰሜን እዝ መከላኪያ ላይ የተቃጣበትን ክህደት ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በአንድነት አውግዘውታል፡፡
ለ2 ደቂቃ በተካሄደው የድጋፍ ስነ ስርዓት ላይ የፌደራል ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ተደርጎ የተውለበለበ ሲሆን የቀኝ እጅን በደረት ላይ በማሳረፍና በማጨብጨብ “እናት ሀገር ኢትዮጵያ” የሚለውን የክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የአንድነት ዜማ ከፍ ባለ ድምጽ ተዘምሯል፡፡
በመጨረሻም እስከአሁን ድረስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ለአማራ ክልል ልዩ ሀይልና ለሚሊሻ አባላት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ድጋፍ ላደረጉና በማድረግ ላይ ለሚገኙ አካላት ምስጋና ቀርቦ የእለቱ ፕሮግራም ፍፃሚ አግኝቷል፡፡