Notice

ዩኒቨርሲቲው የአብክመ ጤና ቢሮ ባዘጋጀው የውይይትና የኤግዚቪሽን መድረክ ላይ ተሳተፈ

News

ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ ከፍተኛ አመራሮችና የጤና ቢሮ ሀላፊዎች፣ በክልሉ ውስጥ ያሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም የውይይትና የኤግዚቪሽን መድረክ ተካሂዷል፡፡

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲም በክልሉ ምክር ቤት አዳራሽ በተዘጋጀው የውይይትና የኤግዚቪሽን መድረክ ላይ ተሳታፊ ሆኗል፡፡ ኮቪድ-19 በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ማለትም የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች፣ የማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፎች፣ የጥናትና ምርምር ስራዎች እና ሌሎችንም ተግባራትን የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቪሽን አሳይተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲያችንም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ባለፉት 10 ወራት በስፋት የተከናወኑ የማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፎች፣ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች፣ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚገልፅ አውደርዕይ አሳይቷል፡፡ በተጨማሪም በአንኮበርና ሸዋሮቢት የምርምር ጣቢያዎች እየተሰሩ ያሉትን የጥናትና ምርምር ስራዎች፣ የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፎችን እንዲሁም በደብረብርሃን ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተደረጉ ድጋፎችን በዝርዝር የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቪሽን በኢፌደሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስተር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ በአብክመ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና በሌሎችም አመራሮች የተጎበኘ ሲሆን አጠር ያለ ገለፃም ማድረግ ተችሏል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ላበረከተው አስተዋፅኦ የምስጋና ሰርተፍኬት ከክልሉ ጤና ቢሮ ተበርክቶለታል፡፡