Notice

ደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ 7ኛውን ሀገር- አቀፍ የባህል ዓውደ ጥናት እያካሄደ ነው

News

አቀናጅቶ ሰዎች እርስ በርሳቸው በስምምነትና በኅብረት ተፋቅረው እንዲኖሩ የሚያደርግ ህግ ወይም የሰላም መሳሪያ ማለት ነው፡፡ባህል የሰዎችን ሕይወት በልዩ ልዩ ምክንያት እንዳይሰናከል በጎዎችን እያጠነከረ መጥፎዎችን እየተወ የማኅበረሰብን የመኖር ዋስትና የሚያረጋግጥ ቀጣይ ሕይወት አኗኗርንም በተስፋ የሚያለመልም መፅናኛ ነው፡፡በተያያዘም የአውደ ጥናቱ ዓለማ ባህላችን ለሀገራችን ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት መሰረት መሆኑን በተለያዩ የምርምር ውጤቶች የምንረዳበት ጠንካራና ሙያዊ ሃሳቦችን በመቀበል ወደፊት የተሻለ ለመሥራት መነሻ የምናገኝበት ሀገር በቀል እውቀቶችን ለማሳደግ ምክክር የምናደርግበት ልዩ ዓመታዊ ጉባኤ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ሒሩት ካሳው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባህላችን ካለው እምቅ አቅም ሊፈጥር ከሚችለው ሀብት፣ የገፅታ ግንባታ፣ሊቀጥር ከሚችለው የሰው ሀይል፣ ሊያስተናግድ ከሚችለው የኢንዱስትሪ አቅም አንፃር፣ሊያመጣ ከሚችለው ማህበራዊ ትስስር፣ ሀገራዊ መግባባትና ፖለቲካዊ መረጋጋት አኳያ ሲመዘን አሁን እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም ብለዋል፡፡

በዓውደ ጥናቱ ላይ የኃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ምሁራን፣ የደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች፣ በዞኑ የሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡