Notice

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለ15ኛ ዙር ተማሪዎችን አስመረቀ

News

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ዩኒቨርሲቲዎች በአካባቢያቸው ባለው ሰብአዊና ቁሳዊ ሀብት ላይ የበለጠ ትኩረት አድርገው በመሥራት በተግባር የተደገፈ ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት እና ዓለማቀፋዊ ይዘት ያለው ጥናትና ምርምር በማካሄድ እምቅ ሀብቶችን በማልማት ለሀገሪቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉበት ሁኔታ ለመፍጠር የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የልህቀት ማዕከልን መሠረት አድርገው እንዲሠሩ የዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮና በትኩረት መስክ ለይቷል ብለዋል፡፡አያይዘውም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲም በልየታው ከፍተኛ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ምሩቃን የሚወጡበት የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ /University of Applied Science/ ሆኖ ተመድቧል፡፡ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2022 ዓ.ም በሃገሪቷ ካሉ የተግባር ዩኒቨርሲቲዎች በተግባር ተኮር ትምህርትና ምርምር ግንባር ቀደም ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ራዕይ አስቀምጦ በኢንጅነሪንግ እና ኮምፒውቲን፣በጤና፣በከፍታ ግብርናና በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ መስኮች ስልጠናዎችና የሰው ኃይል ልማት ላይ አቅዶ የሽግግር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የሶሻል ሳይንስና ሂውማኒቲ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጆች የጋራ ኮርሶችን እያስተማሩ የሚቀጥሉ ኮሌጆች እንደሚሆኑ ጠቁመዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ ይፍሩ ታፈሰ (ዶ/ር)  የኢትዮጵ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲቲዩት ም/ዳይሬክተርና የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ም/የቦርድ ሰብሳቢ እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ ደሀ ብትሆንም በበርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ብትፈተንም በትምህርት ሂደቱ ላይ እየሰራች ያለችውን በርካታ ስራዎችን አጠናክራ ቀጥላለች ብለዋል። ሀገራችን በትምህርት ላይ የምታደርገው ኢንቨስትመንት በእውቀትና በክህሎት የበለጸገ የሰው ሀይል ለሀገራዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ነው ያሉት እናንተም የዚህ ሰፊ ኢንቨስትመንት ውጤት በመሆናችሁ በሰለጠናችሁበት የሙያ መስክ ስራን ከቀጣሪዎች በመፈለግ ብቻ ሳይሆን የሥራ ፈጣሪ በመሆን ለሀገራችሁ ሁለንተናዊ ለውጥና እድገት የበኩላችሁን በመወጣት ታሪክ ሰሪ እንድትሆኑ ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም ስራን በወሬ ሳይሆን በተግባር የምታረጋግጡ፣ ህዝባችሁንና ሀገራችሁን በቅንነት፣ በታማኝነትና በታታሪነት የምታገለግሉ በሥራ ዘመናችሁ ሁሉ የመፍትሄ አመንጪ እንጂ ችግር ፈጣሪ እንዳትሆኑ ሲሉ ተናግረዋል። ለቀጣይ የህይወት ምዕራፍ ጅማሮ ከወዲሁ ዝግጅት በመጀመርም እስከአሁን ያካበታችሁትን እውቀት፣ ክህሎትና ጥበብን ሰንቃችሁ በገጠመኞቻችሁ እየተፈተናችሁ ህዝባችሁን ከወዲሁ ለማገልገል መዘጋጀት አለባችሁ ብለዋል።
በአጠቃላይ ከሴት ተማሪዎች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው የ2015 ዓ.ም ተመራቂዎች  3.995 ውጤት በማምጣት ከፋርማሲ ትምህርት ክፍል የሁለት ድርብ ዋንጫ ተሸላሚ የሆነችው አሚና አህመድ በቤተሰብና በመምህራን ድጋፍ ለዚህ ውጤት እንደበቃች ተናግራለች፡፡አያይዛም ተመራቂ ተማሪዎች ስራ ጠባቂ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑም ምክሯን ለግሳለች፡፡

Images
News gallery News gallery News gallery News gallery