Notice

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳንይስ ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ

News

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም የተጀመረው የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳንይስ ብሔራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቋል፡፡በዩኒቨርስቲው ዋናው ግቢና በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓሶች ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እየተሰጠ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ  ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ ገልፀዋል።ፕሬዚዳንቱ ተማሪዎቹ በጥሩ ስነ-ምግባር ፈተናቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸው ዩኒቨርሲተው ከአምናው ልምድ በመውሰድ የተሻለ ዝግጅትና አቀባበል አድርገን ስለነበረ  ተፈታኝ ተማሪዎች  ደስተኞች እንደነበሩና መልካም ስነምግባር ያላቸው  መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ጥሩ ስነ-ምግባር የመጣው በትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ሱፐርቫይዘሮች፣በወላጆች፣በተማሪዎች፣በማህበረሰቡና በአጋር አካላት ጥረት በመሆኑ ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት ከ10 ሽህ በላይ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን በመጀመሪያው ዙር በሰላምና በጥሩ ስነ-ምግባር አጠናቀዋል ብለዋል፡፡ለዚህ ሰላማዊ ለሆነ ፈተና አሰጣጥ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ሁሉም አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ዶ/ር ንጉስ ታደሰ፡፡

የዩኒቨርቲው ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት በዛሬው ዕለት ከደብረብርሃን ከተማ የመጡ ተማሪዎችና ነገ ከጠዋት ጀምሮ ደግሞ ከሁሉም ወረዳዎች የመጡ ተፈታኝ ተማሪዎች ሽኝት ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡

በተያያዘ ከደብረብርሃን ከተማ፣ ከሀገረማርያምና መንዝ ጌራ ወረዳዎች የመጡት ተማሪ ጌታቸው ካሳሁን፣ተማሪ ሙሴ በጋሻውና ተማሪ መሰረት ወንድምነህ እንዳሉት በዩኒቨርሲቲው የተደረገላቸው አቀባበል ጥሩ መሆኑን፣ ፈተናውም በተዘጋጁበት ልክ እንደነበር፣ፈታኞችም ተማሪዎች ሳይጨናነቁ እንዲፈተኑ ድጋፍ ማድረጋቸውንና ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠማቸው ተናግረዋል፡፡ምኞታቸውም ጥሩ ውጤት አምጥተው በቀጣይ ዩኒቨርሲቲ መግባት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡  

ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም

Images
News gallery News gallery News gallery