Notice

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲተ ለ2015 ዓ.ም የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ገለጻ አደረገ

News

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲተ ለ2105 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም ገለጻ አደረገ፡፡በገለጻው ወቅት የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ፣የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ፣የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ወሰን፣ፈታኝ መምህራንና አስተባባሪዎች ተገኝተዋል፡፡


የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ተማሪዎች ሳይረበሹ ተረጋግተው መልካም ውጤት ለማምጣት መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከባለፈው አመት ከተፈተኑት አንጻር የተረጋጉ በመሆናቸው አመስግነው የተፈጥሮ ሳይንስም ተፈታኝ ተማሪዎች በስነ ምግባራችው የተሻሉ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ተፈታኝ ተማሪዎች የ12 አመት ድካማቸው ውጤት እንዲያመጣ ለነገ ተስፋ በማድረግ ጥሩ ውጤት  ለማስመዝገብ  ፈተናችውን ተረጋግተው በመስራት ፤ትኩረታቸውን ፈተናቸው ላይ በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡


የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ በበኩላቸው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ዕድል ተመኝተው ተፈታኞች ፈተናውን በጥሩ ስነ-ምግባር አጠናቀው ዩኒቨርሲቲ የሚቀላቀሉ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡


በመቀጠል ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲው ቆይታቸው ከደህንነት አንጻር ማድረግ  ያለባቸውንና የሌለባቸውን ጉዳዮች፤ ህግና ደንብ ማክበር  እናዳለባቸውና ተረጋግተው ሳይፈሩ ሳይጨነቁ  ፈተናቸውን መውሰድ እንዳለባቸው ፤ሰላምና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ከጎናቸው መሆናቸውን ኮማንደር መስፍን አዳነ ፌ/ፖሊስ ሰሜን ምስራቅ ምክትል መምሪያ ሃላፊ ገልጸዋል፡፡


ዶ/ር ገዛኽኝ ነጋና መ/ር ደጀኔ ሸዋቀና  ተማሪዎች አጠቃላይ ማድረግ ጠንካራ እንዲሆኑ. እንዳይጨነቁ ፣ለፈተናው ዝግጁ እንዲሆኑ፤ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸውና በፈተና ወቅት መያዝ ያለባቸውንና መፈተኛ ክፍሎቻቸውን  በተከታታይ ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም የተማሪዎች አገልግሎት ዲን መምህር አለምነው መልካሙ  በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡ የምግብ፣ የምኝታ፣ የህክምና የመዝናኛ አገልግሎቶች እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ለተፈታኝ ተማሪዎች ስለ በመብትና ግዴታቸው፣ስለጊዜ አጠቃቀም፣የፈተና ወረቀት አጠቋቆር እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮችንና ተዛማጅ ጉዳዮችን አስመልክቶ የፈተና ማዕከል አስተባባሪ አቶ ሙሉ ኣለም መኮነን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በአጠቃላይ በዘንድሮው አመት በ2015 ዓ.ም በአገር አቀፍ 868074 የ12ኛ ክፍል  የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተና እንደሚወስዱ ታውቋል፡፡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታን ተማሪዎች ከሀምሌ 25-28/2015 ዓ.ም ለአራት ቀናት ፈተና ይወስዳሉ፡፡

          መልካም ፈተና እንዲሆንላቸው እንመኛለን
                                 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ

                                     ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም

Images
News gallery News gallery News gallery News gallery