Notice
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ደረጉት አቶ አህመድ መሀመድ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዳሉት የውድድሩ ዋነኛ አላማ የትውልድ የስነ-ምግባር ግንባታ እሴት ስራ በትውልዱ ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኝ ለማስቻልና የመልካም የስነ-ምግባር ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ጥያቄውን ያዘጋጀው የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የሥነ- ምግባር ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ በሶስት ቡድኖች ማለትም በዋናው ግቢ/ ሶሻል ሳይንስ፣ግብርና፣ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ህግ፣ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ፣ኮምፒውቲንግ/፣በአስራት ወልደየስ መታሰቢያ ጤና ካምፓስ/ጤና ሳይንስና ህክምና ኮሌጆች/፣በአጼ ሚኒሊክ ቴክኖሎጅ ካምፓስ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ጀምሮ ተጋባዥ ታዳሚ ተማሪዎች በተገኙበት በግቢ ደረጃ በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄዷል፡፡
የሥነ- ምግባር ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ይሁን ሽፈራው እንዳሉት በተማሪዎች መካከል የተደረገው የተማሪዎች የስነ-ምግባር ጥያቄና መልስ ውድድር አላማው የትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ሂደትን የበለጠ አጉልተው የሚያሳዩ አስተምህሮ ምንነት ግልጽ ለማድረግ እና በዩኒቨርሲው በሚማሩ ተማሪዎች መካከል የስነ-ምግባር ጥያቄና መልስ ውድድር በማካሄድ አሸናፊዎችን በመለየት በዩኒቨርሲቲና በሀገር አቀፍ ደረጃ በመሸለም ተማሪዎችን በማነቃቃት፣ በስነ-ምግባር ዙሪያ የሚኖራቸውን ግንዛቤ እና ተግባራዊነት ድርሻ ለማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የጥያቄና መልስ ውድድሩ በቀጣይ ሚያዚያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለሚሄደው ውድድር አሸናፊዎችን በመለየት ተጠናቋል፡፡